መለሳዊ የመከላከል ዘይቤ | Addis Neger

መለሳዊ የመከላከል ዘይቤ

“ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ ሰዓት እየወጣ በተመሳሳይ ሰዓት መግባቱ የችግሩ ምንጭ ነው” ብሎ የሚከራከር የመንግሥት የሥራ ሐላፊ፣ ለአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር “በእግር መጓዝ በጣም ጥሩ መፍትሄ ነው” የሚል ታዋቂ አትሌት፣ የጋዜጣ ማሳተሚያ ዋጋ መጨመርን በተመለከተ “ማስታወቂያ ያላቸው አይጎዱም” የሚሉ ሚኒስትር ስታዩ (ሰለተጎዱት እየተጠየቁ ስለማይጎዱት እንደመለሱ ልብ ይሏል) ሞያዊ ሥነ-ሥርዐት ማጣት ከላይ ጀምሮ የሚጋባ በሽታ እየኾነ አልመጣም ትላላችሁ?

መለሳዊ የመከላከል ዘይቤ | Addis Neger

…..”ቀዳማዊ ኀይለሥላሴ ሚዲያ በአገራችን በተጀመረበት ሰሞን ሰጡ ሲባል የሰማኹት ቃለ መጠይቅ ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ ሁሌ ትዝ ይለኛል። ጃንሆይ “መመገብ የሚወዱት ምግብ ምንድነው?” ተብለው ሲጠየቁ፤ እንዲህ መለሱ “እንግዲህ እንደ ሕዝባችን ከጾም ውጪ ሲኾን ጥራጥሬ እንበላለን፤ ሽምብራም የወትሮ ምግባችን ነው”። ቁም ነገሩ ግን ጃንሆይ በትክክል የሚበሉትን ተናገሩ አልተናገሩ የሚለው ሳይኾን እርሳቸው ንጉሥ በመኾናቸው ከተራው ሕዝብ የተለዩ አለመኾናቸውን ለማሳየት መሞከራቸው ነው። መሪዎቻችን ይዋሹን ባይባልም ቢያንስ ግን በአገልጋይነት ስሜት ያከብሩን ዘንድ ይገባቸዋል። አለበለዚያ እነርሱስ ምኑን መሪ፤ እኛስ ምኑን ሕዝብ ኾንነው?”

This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s