‹‹ምነው እንደ ጋዳፊ አልወርድም አልክ›› | Reporter Amharic

Interesting stories from “Reporter Amharic”; “Kibur Mnister”/ “Y.E. Minister”- ክቡር ሚኒስትር  columnist:

ክቡር ሚኒስትር  

[ክቡር ሚኒስትሩ በቤተ መንግሥት ለግብፅ ልዑካን በተዘጋጀ ግብዣ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ከእንግዶቹ ጋርም ያወራሉ፡፡]

    ታህሪር አደባባይ ላይ ከአብዮተኞቹ ጋር ሆነሽ ስትጮሂ መልክሽን ያየሁት መሰለኝ፡፡
    አዎን ክቡር ሚኒስትር ከዚያው ነበርኩ፡፡ ነበርኩ ነው፣ ከረምኩ የሚባለው? ዋና ተሳታፊም ነበርኩ፡፡
    መልካም ነው. .  ትግላችሁም ውጤት አስገኝቷል፡፡
    አዎን ሙባረክን አባረርን፡፡ ለእስርም አበቃን፡፡
 

Read More:

ይቀጥል ይቀጣጥልና አሰማምሮ ይደመድማል

[የስብሰባው ቀን ደረሰ፡፡ ግርግር ተፈጠረ፡፡ ቀደም ብሎ የተበተነው የቀኑ ፕሮግራም ሌላ፤ አሁን የተበተነው ሌላ ሆነ፡፡ ሰብሳቢው ሌላ ተናጋሪዎችም ሌላ ሆኑ፡፡ ክቡር ሚኒስትር ስብሰባውን ይከታተሉት ነበር፡፡ በቴክስት መሴጅ]
    እሺ እንዴት እየሔደ ነው?
    ችግር የለም በቁጥጥር ሥር ነው፡፡ ሰብሳቢው የእኛ ሆኗል፡፡
    በጣም ጥሩ . .  .ተቃውሞ አለ?
    አለ፤ ግን የትም አይደርስም?
    ሰብሳቢው አጀንዳው ቢቀያየርም እኔ እቀጥላለሁ ብሎ ማይክራፎኑን አልለቅም ብሏል፡፡
    ቤቱ ምን አለ?
    እየተቃወመ ነው፡፡
    ምን ብሎ?
    ‹‹ምነው እንደ ጋዳፊ አልወርድም አልክ›› እያለ ይስቃል፡፡
    መሳቁን እንደፈለጉት ይሳቁ፡፡ እንትና ጣልቃ እንዳይገባ ግን ተጠንቀቁ፡፡
    ማን?
    !  N A T O!

 **************

More from “ ክቡር ሚኒስትር”:

[የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመወያየት የአውሮፓ ልዑካን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋርም እየተነጋገሩ ይገኛሉ]     እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡
….

[ምሳ ሰዓት ደርሶ ክቡር ሚኒስትሩና እንግዶቹ በቦታው ተገናኝተዋል፡፡ አጀንዳው ግን የተላለፈው ዜና ነበር፡፡]
    እንዴት ነው ነገሩ ክቡር ሚኒስትርእኛ ጫማ ሥር ወድቀን ይቅርታ ጠይቀናል እንዴ?
    አልጠየቃችሁም የተላለፈው ዜናም ስህተት ነው፡፡ በአስቸኳይ እንዲታረምና ይቅርታ እንዲጠየቅም ታዟል፡፡
    መታረሙና ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ፤ ነገር ግን ምን ዓይነት ሙያና ሥነምግባር ያላቸው ሰዎች ናቸው እንዲህ ብለው የሚሠሩት፡፡
    አሁን ወደመጣንበት አጀንዳ እንግባና እንቀጥል፤ ያኛው እንኳን ለእናንተ ለእኛም አስደንግጦናል፡፡ ሙሉ መልስ ይዤ እነግራችኋለሁ፡፡
    እሺ እንቀጥል፡፡
    የተከበራችሁ የአውሮፓ እንግዶቻችን ኢትዮጵያና አውሮፓ የረዥም ጊዜ ግንኙነት አላቸው፡፡ በችግርም ሆነ በደስታም አብረን ተሰልፈናል፡፡ አሁንም በሽብርተኝነት ዘመቻው ላይ አብረን ነን፡፡ እናንተ ግን ይህን ሐቅ ችላ እያላችሁ ከተቃዋሚዎች ጋር ተሰልፋችኋል፡፡ እነሱ የሚሉትን ታዳምጣላችሁ፡፡ እኛ የምንላችሁን አታዳምጡም፡፡
    ክቡር ሚኒስትር እነሱ ያሉትን አናዳምጥም፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን ለመሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ወይ? ብለን እስከመጠየቅ ደርሰናል፡፡ ነገር ግን የሰብዓዊ መብት፣ የፕሬስ ነፃነት፣ በአጠቃላይ የዴሞክራሲና የፍትሕ ጉዳይ በእጅጉ እያሳሰበን መጥቷል፡፡
[ውይይቱ በጥሩ መንፈስ ቀጥሎ የማጠቃለያው ስብሰባ በነጋታው እንዲካሔድ ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ፡፡ ክቡር ሚኒስትርም ማታ ቤታቸው ገብተው እንደገና ዜና ለመከታተል ተመቻችተው ተቀመጡ፡፡ ዜናውም መጣ፡፡ እንደገና አበዱ]

Read More:


    እኔ?
    አዎን እርስዎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
    አሁን በዚህ ሁለት ቀን ያየሁትኮ አገርንና ሕዝብን የሚጎዳ አደገኛ አካሔድ ነው፡፡
    የቆየ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
    እና አንተ የኢሕአዴግ አባል እያለህ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ኢሕአዴግ ናቸው ትላለህ?
    ናቸው አላልኩም . . . ብዬም አላውቅም፡፡
    አልገባኝም፡፡
    ክቡር ሚኒስትር በእኔ አመለካከት ኢሕአዴግ ውስጥ ሁለት ዓይነት ፓርቲ አለ፡፡
    ኢሕአዴግ ውስጥ ሁለት ዓይነት ፓርቲ አለ ነው ያልከው?
    አዎን ሁለት ዓይነት ፓርቲ አለ፡፡
    ገዢ ፓርቲ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሌላ በውስጡ ምን ዓይነት ፓርቲ አለ ልትለኝ ነው?
    ከገዢው ፓርቲ ጎን ለጎን ተቃዋሚ ፓርቲ በውስጡ አለ፡፡
    ተቃዋሚ ፓርቲም፣ ገዢ ፓርቲም በኢሕአዴግ ውስጥ አለ ነው የምትለኝ?
    አዎን! ሁሉንም በውስጡ ያቀፈ ፓርቲ ሆኗል፡፡
    እንደዚህ ዓይነት ፓርቲ ምን የሚሉት ፓርቲ ነው?
    ‹‹ዋን ስቶፕ ሾፕ ፓርቲ››

This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a comment