ሽብር ፈጣሪ ናት – "Shibir Fetari nat"

ሽብር ፈጣሪ ናት፦ ፍቅርም ያሳበዳት
 

“ዓይን የተፈጠረው ሁሉን ለማየት ነው
አንተን አይቶ ሌላ አላይ አለ ምነው!  “
ትቀኘው ነበረ አፍቃሪ ላፍቃሪው
ስለ ውሩ ፍቅር ስለሚጋርደው
*
እሱዋስ አፍቃሪ ናት
ፍቅር ያሳበዳት፤
ሽብር የፈጠራት
እሱዋስ አፍቃሪ ናት
ፍቅር ያሳበዳት
ምርምር መገንዘብ ማወቅ የከጀላት
ሽብር ፈጣሪ ናት
ፍቅርም ያሳበዳት፦
*
ግን፤ ዘመን ተለውጦ አዲስ ፍቅር መጥትዋል
አታማሪ አፍቃሪ ፦እበዱ ተብልዋ ል
ሁሉም እንዲያብድበት አዋጅ ተደንግግዋል
*
ዓይን የተፈጠረው ሁሉን እንዳያይ ነው
ጆሮ የተተከለው  አቤት ለማለት ነው
አፍ የተቀደደው ሆድ እንሞላ ነው
*
 እንደ አፈጣጠሩ ዓይኑን የሚያይበት
እንደ አፈጣጠሩ ጆሮን የሰማበት
 እንደ አፈጣጠሩ አፉን ያወራበ ት፦

ሽብር ፈጣሪ ነው የሚፈረድበት።
ማየት የደፈረ ማየት የከጀለ ማየት የተመኘ
ሲያዩ እያየ እንዳላየ ያየ
እያየ ፦
እይቶ እንዳላየ ሆኖ ወዘተ ፦ወዝቶ ወዛዝቶ አለቃ ያሞኘ፦
አፉን ለመናገር ጆሮውን ለመስማት
ላለቃው ካልሆነ፦ለሆነ ላልሆነ፤ የተጠቀመበት
አይቶ የተመኘ የተመራመረ፦ በነውር በዝሙት

እንደሚያስኮንነው፦  በህገ ሃይማኖት

  
ሽብር ፈጣሪ ነው የሚጠየቅበ ት፦

ሲዖል የሚገባ የሚበየንብት፦
እሪ በይ አዝማሪ ለዘመነ ኦሪት።
ወዮልሽ አፍቃሪ
እንዳታማርሪ
እንዳትቀባዥሪ፦
ዓይን የተፈጠረው ሁሉን እንዳያይ ነው
አለቃውን አይቶ፦ሌላ ማንም ምንም  እንዳያይ ነው
*
“ዓይን የተፈጠረው ሁሉን ለማየት ነው
አንተን አይቶ ሌላ አላይ አለ ምነው፦”
ስትይ  ክተቀኘሽ
ምርምር መገንዘብ ማወቅ ከከጀለሽ
ሽብር ፈጣሪ ነሽ
ፍቅር ያሳበደሽ።

*

“ዓይን የተፈጠረው ሁሉን ለማየት ነው
አንተን አይቶ ሌላ አላይ አለ ምነው?”
ትቀኘው ነበረ አፍቃሪ ላፍቃሪው
ስለ ውሩ ፍቅር ስለሚጋርደው
*
እሱዋስ አፍቃሪ ናት
ፍቅር ያሳበዳት
ምርምር መገንዘብ ማወቅ የከጀላት
ሽብር ፈጣሪ ናት
ፍቅር ያሳበዳት።

እንደ ንገሩማ፦

ብትሰማም ባትሰማም አልሰሜን ንገርዋት

ያ ል ደ ፈ ረ  ሰ ማ  መች ይሻዋል ጥራት
ንጉሥ ትመርቂ ወደሽ ነው ኮማሪት 
አንቺም እሱም እስዋም፦ –እኔም እኒያም ሁሉም፤– የወዲያው ቀርቶብሽ፦ ለዚህ የበቃችሁት!

ህግዋ ነው  የፍጥረት፤  ሽ   ብ   ር    ነ ው   ፈ  ጣ  ሪ ፤  አሸብሮ ፍጥረት

Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s