ተ ረ ሳ ኣ! !እንደገና !

መንግሥት ቢለዋወጥ ፤ ቢባል ሃገር ቀና!?
(Landgrabbing – Ethiopia)
*
ኢትረሃብ ሁሌም እንደገና
(HUNGER 2011)

ልማት ነው ጀግንነት?

……ወይስ ሞት!

ሲነግሱ ሃያ ዓመት?

*

(ፅድቁ ቀርቶብኝ፦በወግ – በኮነኑኝ፦ይሉ

ማቅናት ሆነ ልማት አልሆነም በሙሉ

ከመዝገበ ቃላት ይሰረዝ ዘንድ  ቃሉ
ኢትዮጵያን ከረሃብ ያገናኘው ሁሉ፤
በነበረን በውነት፦
ከፍ ያለ እንኳን ምኞት፤
ምክንያት ተደርድሯል ሆንዋል የህዝብ ብዛት
ላይወጣ ከሃገር ረሃብ ድህነት ሞት፤
እርዱን ድረሱልን ይባላል ሰሞኑን፦የታል ምንተ ዕፍረት?
መንገድ ተዘርግቶ፦ፎቁ ተተርትሮ ከተማ  ግንባታ፤
 ባረብ በህንድ ገንዘብ በምራብ ዕርዳታ
ለምለሚቷ መሬት ለባዕድ አምርታ
በሥልጣኑ መንደር፦የጥቂቶች ገነት ሆናም ሃገሪቷ። )

*
ደ ግ ሞ ም

*

እች ነች ጭዋታ

ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ

  እንዴ?
 

አማረን ጀግንነት?! (1 )
የዛሬው ሰቆቃ ረሃብ ድህነት ሞት፤
ባደባባይ ታውቆ ዓለም እንዲያፍርበት
ሸሽገው ያኖሩት ይፋ ወጥቶ እውነት!?
*

ተረሳ ኣ! እንደገና!

*
ተረሳ እንዴ ትላንት
የባንዲራስ ንቀት
የጨርቃ ጨርቅ ዕውቀት
ታሪክ ከመቶ ዓመት
አለፈው በድንገት!?

ሊያምረን ነው ዘንድሮ የቆየው ጅግንነት
የሚኒሊኩ ድል፦ ያድዋው ጦርነት
ውሃው የዮሃነስ፦ጥናት ከሃይማኖት
ፋሲል ቤተ መንግሥት
ላሊበላ፦ ዕውቀት ቤተ ክህነት
ግእዝ ፊደል ቅኔ ትምህርት
ያክሱም ሥልጣኔ ኅውልት።
ኧረ ያስተዛዝባል መሰንበት መቆየት
ጃንሆይ አልቀሩም በጃፓኑ ምኞት
ባልተሳካላቸው በከሸፈው ዕድገት።
ደርግም ሊነሳ ነው በመልካም አንደበት
በፈረንጁም ቢሆን የመሳቅያ ተረት፤
መንግስቱ ኃ/ማ ቢፈለግም ለሞት
ደቡብ ሱዳን መጣ፤ ይፋም ባይነገር፦ ቤት የሚሠራለት።
ጉድ! ዘንድሮ ነው ማለት!
የስልጣኑ ድብዳብ፦ከርሞ ሲሰነብት፦
እየከጀለን ነው የቆየ ጀግንነት
ከኔ ወዲያ መሪ ተባለ ያላፍረት
በገዛ ኣንደበት።
እንደነገሩማ፦
ትንሽ ሰው ትንሽ ነው፦ በራሱ ይቀላል 
ከቃሉ ይለያል፤ ምንስ ይጠበቃል!
ለማስታወስ ያህል፦
እናቅ የለም እንዴ በርከት ያለ ተረት
“ዶሮ ሲያደርጉ አይታ ፈልጋ ለመሞት”

በያደባባዩ  ደጋግመው እንዳሉት
እስቲ እኛም እንተርት;
የወጋ ቢረሳ
የተወጋ አይረሳ
ውሃ ካፈሰሱት ሀገር ከበተኑት
አይታፈስ መቼም አይገኝ ብልሃት።
ስንቱን አተራምሶ ባገር በጎረቤት፤
ለማን እንዲሆን ነው ይኅ ሁሉ መልክት
ሆቸ ጉድ! ተባለልን ዛሬ፦ እንጣጥ  እንጣጥ  ማለት፦
ባልተገባ ዕብሪት በኢምንት ዕድገት፤
ወይስ ጨዋታ ነው የህሊና ትምህርት
አዲሱ ብልሃት ላለማመን ስህተት፤
የሰሞኑ ምንባብ ተሃድሶ ዕውቀት
አሰሱን ገሰሱን ሸፋፍኖ ለማምረት።
እንደ ተለመደው፦ ይች ሃገር፦ ተላላ ሞኝ ናት
የሠራላት ቀርቶ የሰራላት በላት፤
መልከ ጥፉን ክስተት፦በስም ይደግፉ ተረት፦ 
በተሃድሶ ስም ታሸጎ ለገቢያ የማይራራው አንጀት፤
አይ ንቀት አይ ድፍረት ሥልጣን ለማሰንበት።
ይልቅስ፦ ዕውነቱን ተናግሮ ማደር የመሸበት፤
ሲሆን ለመሀተብ፦ ባይሆን ለህሊና ዕረፍት።
ዳግም ሲደጋገም፤ የፈረንጁ፦ የሚያሰቀው ተረት፤
ደርግ  መቼም ወታደር እኮ ነው፦ ተብሎ ያለቀለት
 የት ያውቃል ብልሃት።
ይልቅስ ጉድ ጉድ የሚያሰኘው፦
ጉድጓዱ እዚህ ላይ ነ ው፤
አይን እጥብ አድርጎ ሲያሞኙ፦ በስመ አንድነት፤
ታድሶ በመጣው፦ ንቃት አይሉት፦ የሰው፦የትውስት፦
 የአይምሮ ንቀት!
በቃ በ ቃ ተ ዉት!
ይህኛውን እንኳን ተዉት….. ለሚያውቅበት!
ፅድቁ ቀርቶብኝ፦በወግ በኮነኑኝ፦ይሉ
ይህም ሆነ ሌላ  አልሆነም በሙሉ
ከመዝገበ ቃላት ይሰረዝ ዘንድ  ቃሉ
ኢትዮጵያን ከረሃብ ያገናኘው ሁሉ፤
በነበረን በውነት፦
ከፍ ያለ እንኳን ምኞት፤
ምክንያት ተደርድሯል ሆንዋል የህዝብ ብዛት
ላይወጣ ከሃገር ረሃብ ድህነት ሞት፤
እርዱን ድረሱልን ይባላል ሰሞኑን፦የታል ምንተ ዕፍረት?
መንገድ ተዘርግቶ፦ፎቁ ተተርትሮ ከተማ  ግንባታ፤
 ባረብ በህንድ ገንዘብ በምራብ ዕርዳታ
ለምለሚቷ መሬት ለባዕድ አምርታ
በሥልጣኑ መንደር፦የጥቂቶች ገነት ሆናም ሃገሪቷ።
*
እስቲ ይሁን ግድ የለም
በተረፈው ገንዘብ
ዓባይም ይገደብ፤
ልናይ  ቆይተናል
ተስፋ አይከለከል፤
አዋቂ እንደሚለው፦ ባይነፈግ እንኳን ሁለተኛም ዕድል፤
ጨዋታ ብጤ ነው፦ ለወሬም አይመስልም፦
ያንድነቱንስ ቀልድ፦በቀና ህሊናም አይገዛውም ማንም፤
ብለን እንደምድም።
*
ቀላል ነው ምክንያቱ፦
ያስታውስ ባለቤቱ….
****
እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
 ባህር ማዶ ያለውን፤
በየፈረንጅ ባንኩ ያከማቸሁትን
ከረሃብ፦ ከድሃ  ጉሮሮ ቀምቼ፤ እሮሮ  አምርቼ
ት ነው ያልኩትን።
*
Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s