INCIPIT ZARATHUSTRA…ፍካሬ ዞራሳተር

ማስታወሻ

ኒቼን ማንበብ ለውስጠ ወይራው ነው!

ሁሉም ለኔ፤ የኔ  ስለሚለው።

ካልሆነ አይበጅም

አይሆንም ለፈላስፋ ልጅም፤

ሲሉ ከዚህ ጋር አስተያየት መተው ያስፈክጋል!

 

ለአማርኛው ውክፔዲያ / ነጻው መዝገበ ዕውቀት ደራሲ ከምስጋና ጋር።

አንድ ሁለት ምእራፎችን ቀንጨብጨብ አድርገን እዚህ ላደባባይ ገልጠነዋል።

 

ፍካሬ ዞራሳተር

የዞራስተር ፍካሬ: ወደ ሁሉምና ወደ ማንም በፍሬድሪች ዊልሄልም ኒሺ የተደረሰ የፍልስፍና ልቦለድ* ነው። መጽሐፉ በ1883 እና 1885 (እ.ኤ.አ) መካከል በ4 ክፍል የተደርሰ ሲሆን በጊዜው ይሰራበት ከነበረው የአስተሳሰብ ዘዴ ለየት ባለ መልኩ የፍልስፍናን እና የግብረገብን ጥናቶች መርምሯል። የመጽሃፉ አትኩሮቶች፡- የዘላለማዊ ምልልስኃይልን መፍቀድ (*ፈቃድ እዚህ ላይ ጠንካራ ፍላጎት ማለት ነው)፣ የአምላክ በጊዜው በነበሩ አውሮጳውያን ልብ ውስጥ መሞት፣ ስለዚህም የአዳዲስ ዋጋ ወይም ህግጋት አስፈላጊነት፣የበላይ ሰው (*በኒሺ አስተሳሰብ የሰው ልጅ በጦጣወችና በበላይ ሰው መካከል ያለ ፍጡር ነው) መምጣት ትምህርቶች ነበሩ። [1] ጽሁፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ ስልት ይከተል እንጂ የውስጡ ፍሬ ነገር ግን የክርስትናአይሁድ ሃይማኖቶችን መሰረታዊ እምነቶች የሚጻረር ነበር። ኒሺ ይህን መጽሐፍ ” ከሰወችና ከጊዜ 6000 ጫማ” እርቆ እንደጻፈ ይናገራል፣ ማለቱም የመጽሃፉን ሃሳቦች በተራራ ላይ እያለ እንዳገኛቸው ለማስገንዘብ ነበር።[2]

*

*

*

ሶስቱ ሽግግሮች

 • ሌላው የዚህ ክፍል ዋና ሃሳብ ሶስቱ ሽግግሮች ናቸው፡፡የሰው መንፈስ እውነቱንና እራሱን ለማወቅ 3 ከባድ ለውጦች እንደሚያካሂድ ዞራስትራ በዚህ ክፍል ሲያስረዳ፦
” እነሆ ነፍሳችሁ ሶስት ጊዜ ይሻገራል፡ እንኪያስ ግመል ነበራችሁ፣ ግመሉ አምበሳ፣ በመጨረሻ አምበሳው ህጻን ልጅ!”

ትርጉሙም የመጀመሪያው የመንፈስ ለውጥ ወደ ግመል ሲሆን ይህም “ትሁት መንፈስ”ን ያመላክታል፡ እራስን መካድ፣ በሃብት መቆጠብን፣ መታዘዝንና ችግርን መቋቋምን። ይህም ግመልን እራሷን ዝቅ አድርጋ የጭነት እንስሳ እንደሚያደርጋት ባህርይ ነው።

ጫን ያለበት መንፈስ እንዲህ ይጠይቃል “ከሁሉ ነገር ከባዱ ምንድን ነው?” መልሶም “በጫንቃየ ላይ ጭነቴን አዝየ በጥንካሬየ ሐሴት ማድረግ አይደለምን? እራሴን በማዋረድ ኩራቴን መግደል አይደለምን? የዋህነቴን በማጋነን ጥበቤን መፎተት አይደለምን?”

ከዚህ የግመል አለም ወደ አንበሳነት የሰው መንፈስ ለሁለተኛ ጊዜ ይሻገራል። በዚህ ጊዜ ከጭነት ነጻ ይሆናል፣ ከላይ ወደታች በተዘርጋ የሃይል አሰላለፍ ቁንጮውን ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፣ ራስ ገዝ ሆኖ ነጻነቱን በራስ ገዝነትና በሃያልነት ይደነግጋል። በታላቁ ዘንዶ ላይ ጦርነት ይክፈታል፣ የቀድሞውን ግብረገብ ጽንሰ ሃሳብ አውልቆ ይጥላል።

“ለራሱ ነጻነትን ለመቀዳጀት፣ በህግጋት ላይ ሳይቀር “እምቢ” ለማለት፣ ወንድሞች፣ ለዚያ ለዚያ አንበሳ ያስፈልጋል። አዳዲስ ህግጋትን የመፍጠር መብት እንዳለ ለማወቅ ለተሸካሚና ለአክባሪ ነፍሳት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ይህ ተግባር ለነዚህ እንደ ማደን እና የሚታደን እንስሳ ስራ ነው።”

አንበሳ እንግዲህ የነበረውን እምቢ በማለት የሚያፈርስ እንጂ አዲስ የሚፈጥር አይደለም። ስለሆነም የሰው መንፈስ አዳዲስ ህግጋትን ለመፍጠር ለ3ኛ ጊዜ መሻገር ይኖርበታል። በዚህ የመጨረሻው ሽግግር መንፈሱ ከአንበሳ ወደ ህጻን ይቀራል። ህጻኑ አዲስ ጅማሬን፣ ንጹህ የዋህነትን የሚወክልና የድሮወቹን ህግጋት ድል ካደረገ በኋላ አዲስ ዋጋወችን ፈጣሪ ይሆናል።

“ሕጻን የዋህነት ነው፣ ያለፈውን መርሳትም ነው፣ አዲስ ጅማሬ፣ ጨዋታ፣ እራሱን የሚያሽከረክር ጎማ፣ የመጀመሪያ እንቅስቃሴ፣ ቅዱስ የሆነ “አወ-ማለት”። አወ! ወንድሞች፣ የፈጠራ ጨዋታ ቅዱስ የሆነ “አወ” ማለትን ይጠይቃል፡ መንፈስ የራሱን ፈቃድ ይፈቅዳል፣ አለሙን ያጣ እንግዲህ የራሱን አለም ያገኛል።”

ሁሉ ነገር በህጻን ልጅ ተጀምሮ እንደገና በህጻን ማብቃቱ የኒሺን የዘላለም ምልልስ ጽንሰ ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነው። በዚህ የዘላለም ድግግሞሽ የሰው ልጅ እራሱን በማሽነፍ ከነበሩበት ድክመቶች ሁሉ ነጻ በመውጣት አዲስ አይነት ሰው — የራሱ ህግ/ዋጋ ያለው የበላይ ሰው ይፈጥራል።

እኒህን ነጥቦች ለተመረጡ ተከታዮቹ ካስተማረ በኋላ ዞራስተር ወደተራራ ዋሻው እንደተመለሰ መጽሃፉ ያትታል። የዚህ ምክንያቱ ያለሱ ተጽዕኖ ተከታዮቹ በራሳቸው ውሳኔ የራሳቸውን ሃሳብ እንዲያዳብሩ ነው። አስተማሪነቱን ማቆሙም ይህን የፍልስፍናውን ግብ ላለማጣረስ ነበር።

***

***

***

Also sprach Zarathustra

 

Thus Spoke Zarathustra

is a philosophical novel by the German philosopher Friedrich Nietzsche, composed in four parts between 1883 and 1885.

Source: Wikipedia, the free encyclopedia

ከፍካሬ ዞራስተር የተወሰዱ ጥቅሶች

 • ህይወትን የምናፈቅር መኖርን ስለተለማመድን ሳይሆን ማፍቀርን ስለተለማመድን ነው።
 • በፍቅር ውስጥ ሁል ጊዜ ዕብደት አለ። በዕብደት ውስጥ ደግሞ ሁልጊዜ ምክንያት አለ።
 • አንቺ ታላቅ ኮከብ! ፍንትው ብለሽ የምታበሪላቸ ባይኖሩ ደስታሽ ምኑ ላይ ነበር?
 • መብረርን የሚማር ሰው መጀመሪያ መቆምን፣ ከዚያም መራመድን፣ ብሎም መሮጥንና ዛፍ መውጣትን እንዲሁም መደነስን መማር አለበት፣ አንድ ሰው ወደ መብረር መብረር አይችልም!
 • እውነትን መናገር – በጣም ጥቂት ሰወች ይችላሉ! ከነዚህ ከሚችሉት ግን የሚፈፅሙት የሉም`!
 • ደፋር፣ ደንታ የሌለው፣ ተሳዳቢ፣ ጸበኛ– ጥበብ ከኛ እኒህን ትፈልጋለች፡ ሴት ናትና የምትወደውም ጦረኛን ብቻ ነው።
 • እራሱን የማያዝ መታዘዝ አለበት። ብዙወች እራሳቸውን ማዘዝ ይችላሉ፣ ነገር ግን ለራሳቸው ከመታዘዛቸው በፊት ብዙ ይጎላቸዋል!
 • ማህበረሰብ ተኩላውን አላምዶ ውሻ አደረገ። የሰው ልጅ ከሁሉም በላይ ለማዳ እንስሳ ነው!
 • አንድ ትውፊት አጀማመሩ በሩቅ የዘመን ጭጋግ እየተሸፈነ ከሄደ፣ አመሰራረቱም እየተምታታ ከመጣ – በክብር እያደገ ይሄዳል። ክብሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየጨመረ ይሄዳል። በመጨረሻ ትውፊት ቅዱስ ይሆንና በሰወች ዘንድ ድንቅ ይሆናል።
 • ሰው በንዴት አይገልም፣ በሳቅ እንጂ።
 • በቁመና ለማደግ፣ ወደብርሃንም ለመጠጋት በተፈለገ ጊዜ፣ ስርን ወደ መሬት መላክ ያስፈልጋል፣ ወደ ድቅድቅ ጨለማው፣ ወደ ጥልቁ – ወደ መጥፎው።
 • እውነተኛ ወንድ ሁለት ነገር ይፈልጋል፡ አደጋና ጨዋታ። ለዚያ ሲልም ሴትን ይፈልጋል፣ ከሁሉ በላይ አደገኛ የሆነች መጫወቻ።
 • “የታላላቆቹ ተራሮች አመጣት ከየት ይሆን?” ብየ ጠይኩ። ከባህር እንደመጡ ደረስኩበት፣ ማስረጃውም በአለቶቻቸውና በከፍተኛ ገጽታቸው ተጽፎ ይገኛል። ታላላቅ ከፍታወች የሚመጡት ከታላላቅ ጥልቀቶች ነው።
 • ነጻ ከምን? ለዞራስተር ደንታ ይሰጠው ይመስል! ይልቁኑ ብሩህ አይኖችህ እንዲህ ይበሉ፡ ነጻ ምን ለማድረግ?
 • ሳንደንስበት ያለፈን ቀን እንደጠፋ ቀን መቁጥር ይገባል። እንዲሁ በሳቅ ያልታጀበን እውነት ውሸት ማለት ይገባል።
 • መተኛት ቀላል ጥበብ አይደለም፡ ለዚህ ሲባል ቀኑን ሙሉ መንቃት ግድ ይላል።
Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s