ሕብረ፥ቅላጼ


ሕብረ፥ቅላጼ
የሕይወት ትርጉሙ / ፍሬ ነገሩ
ሕይወት ማለት፣
የእግዚአብሄርን፣ ማለትም የፈጣሪነትን ብቃት በሁሉም የተፈጥሮ ጉዳይ ውስጥ እየቀሰቀስ፣ሰብዓዊ፣ ሁለንተናዊ ና የሰው ዘር ኪነ፥ውበታዊ ተፈጥሮን የሚያድስ፣ አያሌ ዘርፍ ያለው የተወሳሰበ የተፈጥሮ ሂደት ነው። የዚህም ማሳረጊያ ግቡ፣ብዙ ትውልድን እያሸጋገረ በህብራዊነት የሚካነውን የሰው ልጅ መፍጠር ነው።/1
የሕይወት ፍሬ ነገር የሚገኘው፣
1ኛ፣ በማህበራዊ መስክ
2ኛ፣ በባህላዊ መስክ
3ኛ፣ በቁስ፥አካላዊ መስክ
4ኛ፣ በመንፈሳዊ መስክ
ውስጥ ሲሆን፤ እነዚህን የሚያዋስኑ መለኮታዊ ድንበሮች ደግም  አሉ፥
5ኛ፣ ክእነዚህ መስኮች አብራክ ወጥቶ የሚከሰተው፣ የሰው፣ ልጅ መስክ እና
6ኛ፣ ከሁሉም መስኮች ጋር ተዛምዶ የሚስተጋበረው፣ ሁለንተናዊ መስክ;።
(Planes: “the conjunctive syntheses”/2)
(መስኮች፣ በሚያያይዙ ማስተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ)
ለእነዚህ መስኮች፣ እንደ ጀርባ ምሶሶ ሆነው የሚቆሙና የሚያገለግሉ ስምንት አድማሶች ወይንም መለኪያውች አሉ።
(Dimensions: “the connective syntheses”/2)
( አድማሶች፣ በሚያያይዙ ማስተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ)
1ኛ፣   ስነ፥መንግሥትና ሕግ
2ኛ፣  ማህበረሰብ ና ስነ፣ምግባር
3 ኛ፣ ቤተሰብና  ፍቅር
4ኛ፣ የሰው፥ልጅ ና ተስፋ፥ብርሃኑ
5ኛ፣ የሰው፥ዘርና ሕሊና
6ኛ፣ ስነ፥ፍጥረትና  ሃይማኖት
7ኛ፣ ሰማያታትና ዕምነት
8ኛ፣ እግዚአብሄር/ ሁለንተናዊነት ና ምሕረት
በነዚህ አድማሳት መሃከል አያሌ የሚያወራረሱና  የሚያጠላለፉ አገናኝ ከፍሎች ሲኖሩ፣ እየተቀባበሉ እርስበርስ የሚያነቃቁ መስተጋብሮችም አሉ።
(Cross‐sections: reflective syntheses)
(ተወራራሽ ፥ ክፍሎች፣ በሚስተያዩ/ በሚመዛዘኑ ማስተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ)
እነዚህ አድማሶች የየራሳቸው ማዕከላዊ ምሶሶ / የሚስቡ፣ የሚወደዱ ልዩ ቁም ነገሮች/ አሏቸው።
(Axes: “the disjunctive Syntheses” /2):
(ማዕካላዊ ምሶሶዎች፣ በሚያለያዩ ማሰተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ)
1ኛ፣ ሰብዓዊነት (ሰ)
2ኛ፣ ስነ፥አይምሮ/ ንቃተ፥ሕሊና (ሕ)
3ኛ፣ ኪነት (ኪ)
4ኛ፣ መድረሻ፥ግብ (ግ)
5ኛ፣ ቁሳቁስ (ቁ/m)
6ኛ፣ ስነ፥ሃይል (ሃ/E)
7ኛ፣ ብርሃን (ብ/c)
8ኛ፣ ምንጩ (ም)
ተመራማሪው አይንስታይን ስለ ስነ፥ሃይል፣ብርሃንና ቁሳቁስ ያገኘውን ማመዛዛኛ/ ፎርሙላ/፣
ባንድ በኩል፣ (በእግዚአብሄሩ ከፊለ፥ዓለም ውስጥ ብለን ለምንሰይመው) ለቁስ፥አካላዊውና  ለመንፈሳዊው መስኮች ማመላከቻ አድርገን ብንወስደው፤
E=mc2 ; Energy = Mass x (Speed of Light)2
ቁሳቁስ፣በብርሃን ፍጥነት እጥፍ ጊዜ ቢባዛ፤ ስነ፥ሃይል ን ያክላል ብሎ መመዘን ይቻላል ማለት ነው።
= ቁ *ብ *ብ
በሌላ በኩል ደግሞ ፣ ለማህበራዊው ስነ፥ፍጥረ ት መገንዘቢያ ይሆን ዘንድ ፣ (የሰው፥ልጅ ሌላው ከፊለ፥ ዓለም ብለን በምንጠራው) ለማህበራዊውና ለባህላዊው መስኮች፣ ተመሳሳይ ማመዛዘኛ ማስቀመጥ ይቻል ይሆናል።
I= hq2 ; Intelligence = Humanity x (Quality of Music)2
አንድ የሆነ፣ ሰብዓዊ የህሊና፥መመዘኛ (ሰ)፣ በስነ፥ ኪነት  ረቂቅነት(ኪ) እጥፍ ጊዜ ቢባዛ ወይንም ቢገናኝ፤
ለስነ፥አይምሮ (ሕ) ከብርና ክብደት ማለካኪያ ይሆን ይሆናል ለማለት ነው።
=  ሰ* ኪ* ኪ
በዚህ የአመለካከት ዘይቤ/ ሞዴል፣ በአራቱ መስኮች መሃከልና በየራሳቸው በየመስኮዎቹ ውስጥ ሕብራዊነትን/
ሕብረ፥ቅላጼን እያስተናገዱ፣ በየመስክ፥ዘርፉ ያሉት ከፍተኛ የሰው ልጅ ዓላማዎች ላይ መድረስ ነው፤
የሕይወት ትርጉሙ።
እነዚህም፥
ሰላም፣ ሰብዓዊ ባህል፣ ፍጹማዊነት/ሃብት እና ፣ ዕምነት
ናቸው።
እነዚህ ዓላማዎች የሚሳኩትን ያህል፣ ሕብረ፥ቅላጼው፣ በእግዜር ምስል የሚከሰተውን የሰው ልጅ ፥ ማለትም መድረሻ፥ግቡ ላይ ደርሶ ከ ምንጩ ጋር ለመግጠም ዝግጁ ይሆናል። ዛሬ ያለንበት ዘመን ግን፣ ጊዜው አሳዛኝና ይልቅም በፀረ፣ሕብራዊነቱ የተሞላ ነው። ይህ  የዛሬው ዘመን የሚያሳዝነው የሆነው፣ ፀረ፣ሕብራዊነቱ፣ በሕይወት መስኮቹ መሃከልም ሆ ነ  በራሳቸው በየመስኮዎቹ ውስጥም ፀረ፣ሕብራዊነቱ ስለገነነ ነው።
****
1).Reformulated after an encounter with .complexity theory…and further philosophical survey
(cf. Original intuition, 1/2006).
2)  .Connective, conjunctive and disjunctive  syntheses. concepts from Kant, whitehead and Deleuze, as interpreted
by Steven Shaviro, http://www.shaviro.com; and my fourth one, what I call reflective syntheses
Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s