ማድ፥ቤት ለመረጠው

ማድ፥ቤት ለመረጠው፣ ጨዋታ ባለበት
ለቀልድና ነገር ይህ ይደረስለት፥
*
ዘራፍ ዘራፍ በሉ፣ ኧረ እንኳን ደሳለህ
መለኪያ ሳትይዝ ጨዋታ ላማረህ፣
ሰውን አስጠልቶ ከማድ ቤት ላስቀረህ
ተመስገን ሳትለው አምላክ ለፈጠረህ፤
እኔስ መለኪያዬን እንደሰጠኝ ልቆይ
ከሰውም አይለየኝ ከምልበት እ ፎ ይ፤
ቅኔን ከማህሌት፣ የምቀኛኝበት
ማን ይሆን ተረኛ፣ ማነሽ ባለሳምንት፤
እየተባባልኩኝ የምቀልድበት፤
ቀን እስካለ ድረስ፣ ግብ የምመታበት፣
ሁሉንም እንደ ኳስ የምጫወትበት፤
ሰው ሙሉ በሆነው ያገር ልጅ ባለበት፤
በተራዋ እስክታልፍ እችኛዋም ሕይወት።

*
ከመንገደኛው

Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s