አሁንስ በቃኝ

የማንንም ነፍስ፣ እግዜር ይማር ብንል

እግዜርም ኢትዮጵያን ይታረቅ ይሆ ናል።


ቂም በቀልን ትተን፣

“ይቅርባይነትን” መለኮት ተክነን፤

 

ጸሃዩ ይውጣልን ፣

  ሁሉን ደግ ያርግልን ፤

ለትልቅ ለትንሽ ህሊና ይስጥልን!

*

ክንግዲህስ  ይብቃ፣


ያ ሕዝብ ተሰቃይቷል

ፍዳ በቂ አይቷል

ትእግስትና ሰላም ብልህ መሪ ይሻል።
*********************************************
የበረደው እንደሁ፣

አሁን በቃኝ ብሏል

*********************

(Picture source : Awrambatimes)

እንዳው በሩቅ በሩቅ አጋ.ጣሚ፣ በሰፍራ ከሌለሁ

ይተካኘ በረከት ፍጡም አምነዋለሁ፣

እዚሀ ብቻ ሳይሆን ማዶም እሻዋለሁ፣

ማን ያውቃል አዳሬን፣ ካለልኝ አንድ ሌት ይዤው አሄዳለሁ።
!
ግን ታድያ ይገርማል
በረከት ሲጠራ አቤት ማን ይለኛል፣

የጦር ሚኒስቴሬ፣ ከነአባት የነፍሴ፣

ነገሩ አልገባኝም ፣ ምስጢር ነው ስላሴ፣

ህጉ ባለሁበት፣ ስማ በለው የለ፣ ሁሉም ለቅላጼ።

እናም ልሰናበት፣

አሁንስ

በቃ!

እኔንንም በቃኝ ፣

አለቅም ቢሉኝም ሁለት ወር ይዘውኝ

ጨክኜ  ሄጃለሁ አራምባና ቆቦ እንዳትፈላልጉኝ፤

ዕድሜና በረከት ነፍስ ከሌለበት

ምንም ፋይዳ የለው የቀዝቃዛው እቤት፤

ይብላኝ ለስጋዬ በገዛ ወዳጄ ለተቀለደበት፤

(ዕድሜ አይባል የሉ)

ምህረት ለፓፓሴ ለተገላገሉት

አንድ ቀን ሳይቆዩ ለተሰናበቱት

ለኔም ደረሱልኝ ለስጋዬ ዕረፍት፤

የነፍሱን አናውቅም፣ ቀርቧል አንድዬ ፊት፣

ያሳዝናል ብቻ፣ ፓፓሴም አልበቁ ለአማላጅነት።

ጉድ አንድ ሰሞን ነው፣ ሰላም ከሰፈረ በኢትዮጵያ ምድሪት፣

ማን ያውቃል ርህሩህ ነው፣ለኛም በሰማይ ቤት

ይወርድ ይሆናል የአንድዬ  ምህረት!

ወዳጆቼ በምድር ከተማሩ ትዕግስት፣

እናም ልማጠን መሰለኝ፣ እኔን ለተሳነኝ፤

መልክተኞች ካሉ አደራ በሰማይ ፥ አደራ በምድር፣ ቶ ሎ ይንገሩልኝ!!!

 

 

(እንደገና የታተመ፣ ከሞት አዋጁ በፊት)

*

እምነት ለጎድለው

ለማይቀበለው

ማለፉን አለቃው

ላልተመራመረው

በጠራራ ጠሀይ ፈቅዶ ለሚሞኘው!

አንዲህ ሲል ዘከረው

አልሞትኩ ብሎ ዋሾው!

*

እኛንም አግዜሩ፣ ይቅር ይበለን

ሙት ወቃሽ፣ ስላደረገን!

>>>>>>>>>>>

 

አልሞትኩም ብያለሁ!

ደግሞም ድንቅ እንቅ ይበላችሁ

አልፌ ተርፌ  ሞቼም እነሳለሁ! 

ካስፈለገም ድግሞ ሳልኖር እገዛለሁ፣
 

ለታሪክና ፌዝ ይመዝገብ በቶሎ፦ በጥብቅ አዝዣለሁ

እንዳንረሳሳ  ጅራፍ እባላለሁ

ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
  ብቻ ብያለሁ፤
 
መቼስ እስቲ ይሁን፣ ቀልቤን ገፈፉችሁ፦

   ብቻ እንዳትነካኩ፣ ስልጣንና ሃብቴን፣
ለዘመድ አዝማዴ፣ ባህር ማዶ ያለውን፤  

ከክራይ ሰብሳቢ ያስተራረፍኩትን፣

ከባዕድ ወዳጄ እየፈረንጅ ባንኩ ያከማቸሁትን።


ጠላት ከወዳጄ ባለየበት ዛሬ፣

አደራ ቃሌንም፣ እንዳያንስ  ከ ብ ሬ 

ለታሪክ ትዝታ ይመዝገብ በቶሎ 

በጭር ተቀምሮ  እንዳለው ዝቅ ብሎ

 

*

ሌቱ እስኪነጋ ለት

ቀን እስኪወጣ ለት

ያገሬ ሰው እንደሁ

ተኝ ሲሉት ተኛለሁ

ቁም ሲሉት ቆማለሁ።

 

እኔ ግን እነሁ

አድንቁ ይግረማችሁ 

ቀኔ የሞላ ለት

 ክጫካ ወጥቼ፤

አሜሪካን ወዶኝ

እንግሊዝ ዶልቼ፤

ከተማ ገብቼ፦

  ሃያአንድ ዓመት ጨክኜ ገዛሁኝ

የምሥራች በሉኝ።

ነገም ዛሬም እኔ አርባ እሞ ላለሁ፤

እከርማለሁ ገና  ከንጉሥ እበልጣለሁ፤

ቤን አሊ ጋዳፌ ሙባረክ አይደለሁ

ባስራ ሁለት ቢላ መብላት ተክኛለሁ።

 

እንደኔ ዓይነት ምላስ፤ 

                     ከሰንበር የሚለይ

ባሳብ በትካዜ፤

ባገር በወንዜም ላይ፤

                ኣንድም ቀን አይታይ፤

መለስ ዘና ዘና፤ ደሞም፤

ካስፈለገም

የሚል ቆጣ ቆጣ

የሚያስደነግጥም በጣቶች ቆረጣ፤

                   ሃያ ምላስ አለኝ

በመላው አፍሪቃ፤

                ፍጡም ወደር የለኝ።

ለሁሉም መልስ ያለው፤

                         መለስ እባላለሁ

ባባቴ ዜናዊ  

የዜና ፋብሪካ፦ 

                      ወሬ እወልዳለሁ

ዕጡብ ድንቅ በሉኝ፤ 

                           ዘላለም ኖራ  ሁ።

እንዳው በሩቅ በሩቅ አጋ.ጣሚ፣ በሰፍራ ከሌለሁ

ይተካኘ በረክት ፍጡም አምነዋለሁ፣

እዚሀ ብቻ ሳይሆን ማዶም እሻዋለሁ፣

ማን ያውቃል አዳሬን፣ ካለልኝ አንድ ሌት ይዤው አሄዳለሁ።

*

እንዲያው ከመቅጽበት፣ 

እስቲ፣  ልተዋወቅእኔም  ጅሬ !

 

 

This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s