ከኔ ወዲያ

ዛሬ ጊዜ መቼም ሳጥን የሚወዱ ዓይነታቸው ብዙ ነው።
አንድ ዓይነት ሁሉንም የሚያደርጋቸው ግን አንድ ጉዳይ አለ።
ሳጥን ውስጥ መቅረት ስለሚፈልጉ፣ ሁሉም ከኔ ወዲያ ባዮች መሆናቸው ነው።
እስቲ አማርኛችንም ወደ ሳጥን (1 ከመላኩ በፊት፣
የለም እንዳውም እንዳይላክ ስንል እንናገርበት፥
*

 ከኔ ወዲያ  

ነጋ ጠባ እኔ  ማለት

ትልቅ ምንጩ ፍርሃት

 ሆኖ እኮ ነው ብቸኝነት፤

የሚ-ኖረው ለጥፋት፣ በጥፋት፤

በድክመት፣ ያለምነት፤

ላይቀር ሞት።

ከኔ ወዲያ ማ-ይሙት

እየማለ ሲገዘት

 ምኑን አወቆ ስለ መብት፤

ግማሽ ጽዋው የሚ-ሞላው

መች ባወቀው ይኸኛው፣

ለመሆኑ በዛ ማዶው

በ-ዚያ ሌ-ላው

መች አ-ርቆ አሰበው፣

ከኔ ባዩ የጎደለው

ግማሽ ጎኑ አምላኩ ነው፤

ባምባው ብቻ የማይገነው፤

 ከኔ ወዲያ የማ-ይለው፣

በሁሉም ቤት የሚ-ሆነው፤

                       ለ ዝንተ ዓለም የሚዘልቀው።
*

 (1) ባገራችን የባህልና ታሪክ ቅርስ የሆኑትን  ሁሉ ለማፈራረስ  የመጣብንን የባዕድ ሥልጣኔ አባዜ ለማመልከት ነው። (ፎቶ: በጸሐፊው የተላከ)

This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s