የማን ሆነሽ ትባርኪያለሽ

Graziani

የማን ሆነሽ ትባርኪያለሽ (1


„ እስቲ እቺን ብላልኝ፣
እቺንም ጠጣልኝ፣
ብሎ አሳድጎኝ፤
ኧረ ለመሆኑ 40 ዓመት ሲሞላው
ላባት ልጅ ኣይደርስም ማን ይሆን ያለው ?
አብልቶ ኮትኩቶ ለቀባባኝ አባት፣
ቢሰራስ ቢወደስ የግራዝያኒ ሃውልት
ላልቆምለት ኖሯል ኧረ እንዲያው ማ ይሞት?
እንዴት ዓይነቱ ነው የዛሬውስ ድፍረት
ሰልፍ ካልወጣሁ አለኝ፣ ላለቀ ህዝብ ትላንት
ሀገር አለኝ ብሎ መቶ ዓመት ላልሞላት!“
****
እንዲህ ሲል ነገረህ፣ አሻንጉሊት መንግሥት፣
እንዲገለጽልህ የአበዉ ተረት።
http://www.goolgule.com/misguided/
ያገር ወዳድ ያለህ! ጨዋታው ኧረ ይግባን፣
ያህዮቹ መንደር ፣ ጥርሳችን የነቀልን፣
ኣህያውን እንበል ዳውላውን ንቀን፤
ዳውላው በስብሷል አያድርም አንድ ቀን፣
አህያው ከሌለ ከተወው ሸክሙን።
አህያም አንሻም፣ ዳውላም ይቅርብን፣
እንዳባቶቻችን እንደታሪካችን፣
ፈረስ ግልቢያ እንማር፣ ኧረ ሰው እንሁን።
***
1) እነዚህ መስመሮች ብቅ ያሉት፣ ሃገር ቤት ያሉ ሃገርወዳዶች የግራዝያኒ ሃውልት በአዳባባይ እንዳይቆም በሚሟገቱ ምሁራን አነሳሽነት የተጀመረ እንቅስቃሴን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፈኞች፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ይግረማችሁ ተብለው ወደ ወህኒ ቤት እንደተወሰዱ ዜና ስሰማ ነው።
http://www.debirhan.com/2013/03/dozens-of-anti-statue-marchers-detained.html

ሲሆን በእራሱ በኢትዮጵያ መንግሥት አናሳሽነት የዛሬው የኢጣልያ መንግሥት የሚያደርገውን አሳፋሪ ድርጊት በመቃወም መልዕክት ማስተላለፍ ሲገባ፣ እስተናካቴው በተቃራኒው ሆነ። ያሻንጉሊት መንግሥት ተፈጥሮን ለሚያውቅ ግን ይህ የሚደንቅ አይደለም፣ የማን ሆነሽ ትባረኪያለሽ ነው። ይልቅ እንደዚህ ዓይን ባወጣ መንገድ የኢትዮጵያ መንግሥት የማን አሻንጉሊት እንደሆነ ተረድተን፣የአሻንጉሊት አድራጊዎቹን ደባ ለማጋለጥ ውጭ የምንኖር ሃገርወዳዶች፣ በየመዲናቸው እንደ አንድ ህዝብ ሆነን የምንነሳበትን ዘዴና ብልሃት ብንፈልግለት ይበጃል። የኢህአዴግ መንግሥት ፣መቼም ያለነሱ ድጋፍ እንድ ቀን እንደማያድር ሁሉም ያውቀዋል። ግራ የሚያጋባው ብቻ፣ ይህን ሃቅ በሆዳችን ይዘን፣ አንዴ ሃገር ቤት ህዝቡ አለተነሳም፣ እያልን ከምናኮርፍ፣ ወይንም መንግሥት ተራ በተራ ህዝብ እየከፋፈለ የተቃዋሚ ሃይሎችን እንቅስቃሴ በእንጭጩ ሲቀጭ መርዶ አማላላሽ በቻ በመሆን ብዙ ጉልበት፣ ሃብትና ትምህርት ከምናፈስ ፣ የውጭዎቹ ሃይሎች፣ በተለይም፣የዴሞክራሲ መብቶች ባሉባቸው ሃገሮች፣ አሜሪካና iምዕራብ አውሮፓ ውስጥ፣ “ጥርሳችንን የነቀልን „ ሁሉ፣ የተቀላጠፈ የማጋለጥ ዘመቻ ለማድረግ ለምን እንደማንነሳ ነው።

Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s