እውነት የገብሬል ለት!

https://guzoliyu.files.wordpress.com/2013/03/crowd-of-people-scaled1000.jpg

እውነት !

የገብሬል ለት!

እስላም ክርስትያኑ አንድ የሚቆምበት!

እስቲ እንደ ታሪካችን አንድ ጉድ እናፍላ!

ከንግዲህ እሹሩሩ ምንም የለው መላ!

መርዶና ትንተና ዲስኩርና ምላስ  በቃ ይበቃናል፣

እባቡን ከጭራው ጎትቱ  አስጎትቱ፣ኮንኑ አስውግዙ ስንባል ከርመናል፣

አንድም ፋይዳ አላየን፣ ላርባ ተከፋፍለን 40 ዓመት ሰምተናል።

እስቲ ዘዴ ይግባን፣ ሞቶም ስለማያውቅ እባቡ በጭራው፣

በየካቡ ቆመን፣  ራሱን እናግኘው።

መድሃኔ ዓለም እንደሁ፣  ከ ተ ፍ   የሚለው

ሰላም በነጻነት  ነገ የሚነግሠው፣

ይገባኛል ብሎ፣

ሲቆሞ ባደባባይ ህዝቡ እንዳንድ ሰው!!!!

**********************************************************************************************

ስለ

ኢትዮጵያ በ21ኛው ክፍለ ዘመን

(ተፈሪ መኮንን)

የተገኘ

ሙሉውን ለማንበብ፥

http://www.goolgule.com/ethiopia-in-21st-c/

………

“በሰላማዊ ትግል ግን እንደሌሎቹ፣- እንደ ሙባራክና እንደ ቤን አሊ፣ እንደ ሆኔከርና እንደ እገሌና አገሊት……ወደው ሳይሆን ተገደው  ቤተመንግሥቱን  ጥለው፣እያለቀሱ ፣ የወያኔና ሻዕብያ መሪዎች ይወጣሉ። የማይወጡበት፣ ምንም ምክንያት፣የላቸውም።

በሰላማዊ ትግል፣ እንደሚታወቀው፣  እላይ የተጠቀሱትና ሌሎቹ፣ ብዙ ሕዝቦች ነፃ ወጥተው፣የ ዲሞክራሲን አየር፣ ተንፍሰው፣  አዲስ ሥርዓት መሥርተው፣ መሪዎቻቸውን፣ በምርጫ፣ እያወጡም፣መልሰው፣ አያወረዱም በሰላም ለጓዙ፣ ሊኖሩ ችለዋል። የኢትዮጵያም ጉዞ ወደፊት ከዚህ የተለየ  ሊሆን አይቸልም።  እዚያ ላይ ለመድረሰ፣ ግን ፣ ቢያንስ አንድ አርምጃ በመጀመሪያ፣በየፊናችን „ መንጫጨቱን ትተን“፣  መራመድ፣ይኖርብናል። ደግሞም፣ አለብን። አለበለዚያ ፣ኢትዮጵያ  – በተጀመረው ጉዞ- ነገ አትኖርም።የመኖሩዋም፣ ጉዳይ፣የሚያጠራር ነው።

አለበለዚያ፣ ወያኔና ሻዕቢያ ነገ ታርቀው፣ ጉድም፣ ሊፈላብን፣ ይችላል። ይህ ሁለተኛው፣ምክንያት ነው። ሌላው፣ሦስተኛው ምክንያት፣ በኢትዮጵያ ላይ ወያኔና ሻዕብያ እንዲቀልዱብን ፣ ድጋፍ እየሰጡ፣ ሰበአዊ መብት ሲረገጥ፣ ዝም ብለው፣ (አምኒስቲ ኢንተርናሸናል በየጊዜው ይከሳል) በመንግሥት ደረጃ ግን እነዚህ መንግሥታት እያዩ፣ ለይስሙላ ፣ በዝቀትኛ ባለሥልጣን እያስተቹ፣ የሚያሾፉብንን፣ትላልቅ መንግሥታት፣ ሳንፈራ፣ በአደባባይ፣እነሱን፣እነሱ አንድ ቀን ተነስተው፣ ሳይሸጡንና ሳይለውጡን፣    በሕዝባቸው ፊት የግድ መክሰስ ይኖርብናል።

እኔ አልረሳውም፣ ማንም ሰው፣ አይረሳውም፣ የሞስኮ ኮምኒስቶች፣ ለእኛ፣ እነ፣ ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ና ጭፍሮቹ፣እነሱ ያሻሉላችሁዋል ብለው መርጠውልን፣ አሥራሰባት ወርቅማ ዘመናችንን፣በከንቱ አሳልፈናል። አሁን ደግሞ፣ ይህ አልበቃ ተብሎ፣ይኸው፣ ሃያ አንዱን አመት፣ አሜርካኖቹና እንግሊዞቹ አዲስአበባን፣ ለሕዝባዊ ወያኔ፣ አሥመራን፣ ለሻብዕያ ሰጥተው፣ ያው እነሱ፣ በሌላ አነጋገር፣ መርጠውልን፣ እንደገና መከራችንን እናያለን።

ይህ መቆም አለበት። ይህም ሥራ፣ መታረም አለበት። እኛ ነን፣እንጂ፣አገሪቱን፣ ሊያገለግሉ፣ የሚችሉ ሰዎች፣በየአራት አመቱ መምረጥ ያለብን፣ አነሱ አይደሉም።እኛ ነን መጪው፣ ጠቅላይ ሚንስትር ማን ይሁን ብለን ድምጻችንን፣አደባባይ ወጥተን፣ የምንሰጠው አንጂ እነሱ አይደለም። ይህን ደግሞ፣ ዛሬ ከአልተናገርን፣ ነገ እኛን ከመሸጥ በምንም አይነት አይመለሱም። ያደርጉታል።

ስለዚህ፣  በአሜሪካን አገር፣ በዋሽንግተን ከተማ፣ ልክ፣ ዶከተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ከ አንድ መቶ ሺህ ሰው በለይ አሰልፎ ለጥቁር ሕዝብ ነጻነት፣ ያኔ እንደወጣው፣ ከዚያ የሚበልጥ ኢትዮጵያዊ፣ ዋሽንግተን ላይ ወጥቶ፣ የአሜሪካን መንግሥት፣ ወቅሶ ፣ለአሜሪካ ሕዝብና  ለአለም አቤቱታውን አሰምቶ፣ የአበባ ጉንጉን፣ የሊንከንና የክንግ፣ ሐውልት ሥር አሰቀምጦ፣ ፊቱን ወደ አዲስ አበባ፣ ሰው ሁሉ፣ ማዞር ከእንግዲህ፣  ይኖርበታል። ዘራዕይ ደረስ እኮ፣ ሮም ላይ በፋሺሽቱ ሞሱሌን ላይ፣  -ያውም ነጻነት በሌለበት፣ አገር፣ ጎራዴውን፣ መዞ፣ለነጻነቱ፣ ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ፣ ሮም ላይ ወድቆአል። አሜሪካን አገር እንደምናውቀው፣ ሠልፍ ይፈቀዳል። አሜሪካን አገር፣ ሰው ሐሳቡን መግለጽም፣ ይችላል።

ታዲያ፣ ወደ 50 ሺህ የሚጠጋ ሰው ቢያንስ፣ ለእግር ኳስ ውድድር፣ አሜሪካን አገር የሚወጣ ከሆነ፣ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ፣ መቶ ሽህ፣ ከዚያም በላይ ሰው፣ ሠልፍ የማይወጣበት፣ምንም ምክንያት የለም። ደግሞ አንደዚህ አይነቱ እርምጃ በፕሬዜዳንት ኦባማ የግዛት ዘመን፣ በእሻቸው ሥር መሆኑ፣ትልቅ ትርጉም በታሪክም ፊት፣… በሚዲያም፣…በአፍሪካም፣…በጥቁሮችም ዘንድ፣ ትልቅ ቦታ አለው።

መሰብሰብ ፣ መናገር፣ መጻፍ፣ መቃወምና ሠላማዊ ሠልፍ በሕግ በተፈቀደባቸው፣ አገሮች፣ ኢትዮጵያኖች ተሰብስበው፣ በሁለት ምላስ የሚናገሩትን፣ የአሜሪካንና የአውሮጳን መንግሥታትን፣በሰላማዊ ሠልፍ እበተከታታይ፣ በለነደንና በፓሪስ፣ በስዊዲና በፍራንክፈርት፣በኬንያና በደቡብ አፍሪካ…. ነሱን  መጠየቅ፣  በሕዝቦቻቸውም ፊት፣ ማዋከብ- መብታችን ነው- ይገባል። መሆንም አለበት።

ለሮበርት ሙጋቤ፣ ለጄነራል  አልባሽር፣ ለአህመድ ነጅዳድን….ለበርማ ጄኔራሎችን፣ ….. ለኣሳድ ፣…. ወዘተ ፣ወዘተ፣ መውደቅ፣ ጡዋት ማታ የሚሰሩ፣  ለመተችት እነሱን  የማይደክሙ፣ ዲሞክራሲ ለነዚያ ሕዝቦች፣ በቶሎ  መምጣት አለበት በአደባባይ የሚሉ፣ የምዕራብ መንግሥታት፣ ለምን በወያኔና ሸብዕያ ላይ እንደማይበረቱ፣ አደባባይ ላይ እነሱ፣ በሕዝባቸው ፊት፣ መከሰስና  መጠየቅ፣የግድ፣ ያስፈልጋል። መልሳቸውንም፣ ማዳመጥ፣ ትምህርት ነው።

ከዝያ በኹላ እንግዲህ፣ አዲስ አበባን፣ እህአዴግ የራሱን ሕገ-መንግሥት እንዲያከብር፣  በሠልፍ ማጥለቅለቅ ይቻላል።

እንዴት?

ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ ሳልገባ፣ ሁለት ነገሮች ብቻ ላንሳ። በምንገበያይበት፣ በአሜሪካን ዶላር ላይ፣ አንድ ጥሩ ምን የመሰለ፣ አረፍተ ነገር አለ። „We trust in God“ ይላል። እኛም፣እኮ ገና ዱሮ፣ በእግዚአብሔር፣ እናምናለን፣በእሱም እንመካለን። ስለዚህ፣ ለእኛም፣ መጽሓፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን በእጃችን ይዘን አደባባይ መውጣት፣- አሜሪካን አገር እንደሚደረገው- ወንጀል፣ አይደለም። ወንጄለኛም፣ አያደርገንም።  ይህን ይዘን- ይህ ነው የእኔ ምክር-   መጽሓፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን በእጃችን ይዘን አደባባይ፣…  የገብርኤል ቀን እንውጣ! በአርጀንቲና- ምሳሌ ለመጥቀስ- እናቶች፣ የብረት ድስታቸውን፣ ይዘው ወጥተው፣ የወታደሩን መንግሥት ጥለዋል።

ግን ለምን የገብርኤል ቀን ብቻ?

…..በማሪያም፣ ዕለት፣ይቻላል። በሚካኤልም ፣ በጊዮርጉስም፣…..ዓርብም ቀን ቅዱሳን መጻኅፍትን፣ ቅዱስ ቁራንና መጽሓፍ ቅዱስን  ይዘን እንውጣ!

እመኑኝ፣ ውንድሞቼና እህቶቼ! ከዚህ አይነቱ፣የሰላማዊ ትግል  በኁላ፣ ድብልቅልቁ፣ ይወጣል።”

…………

http://www.goolgule.com/ethiopia-in-21st-c/

(የጎሉትና እንዲታዩ ወደ ጎን የተመለከቱት በእኔ ነው!)

Advertisements
This entry was posted in ማህበራዊና ባህል/በአማርኛ, standard. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s