እነ ማን ነበሩ ? …እ ስ ቲ ይሁና ……

Scapegoating***

እነ ማን ነበሩ ? የሚል ምዕራፍ ውስጥ  ቦ ታ የሚሹ ኢትዮጵያውያን !

ብርሃነ መስቀልና ሃይሌ ፊዳ !!! *1

መቼም ሆነ መቼ የፖለቲካ ጉዳይ ያገባኛል የሚል፣  ያለፈውን፣ ከርሱ፥ከዛሬው በፊት ያለውን በበቂ ያላጠናና ያላገናዘበ፣  ሲሆንም አስፈላጊውን ተመክሮ ያላዋሃደ፣ ትክክለኛ የዛሬው የፖለቲካውን  ፈር ያገኛል ማለት ዘበት ነው፣ እንኳን ነጻ ወጥቶ ነጻ ሊያወጣ ቀርቶ፣ ያልሆነ ሃይል ወይንም ያኋላ ኋላ ወደ ባሪያነት የሚቀይረው የባዕድ አሻንጉሊት ነው የሚሆነው!

የኛ ትውልድ፣ የኔ ትውልድ፣ ከሚያደነቁረው የኛን ሀገር ብቻ ሳይሆን ዓለምን በሙሉ፣ በተለይም የወጣቱን አእምሮ የሰለበው ቀኖናዊ ርዕዮተ ዓለም (አምባገነንነት የሚሰብከው ኮሚኒዝም፣ ከወዝ አደሩ ሙሉ ሥልጣን በተፈጥሮ ተሰቶኛል የሚሉ የግለሰቦች አምብገነንነት) ሰለባ  መሆን ብቻ ሳይሆን፣  ትልቁ ድንቁርና  ያለፈው ታሪካችንን ረጋ ብሎ ለመረዳት ያለመሞከርና በቀኖናዊ ርዕዮተ፥ዓለም፣ (ለኢትዮጵያ የሚሆን ሀገርወለድ ርዕዮተ ኢትዮጵያን ከማፈለለግ ይልቅ) የእውር የድንብር መነዳታችንና መንዳታችን ነበር። ዛሬ መጨረሻው ባይባልም፣ የደረስንበት ውርደት፣ የኢትዮጵያው ሲያንስ፣ ሰሞኑን በዓረብ ሃገሮች የሚደርሰው ውርደትና፣ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው፣  ከየትም ወገኑ አልወገኑ ፣ ምን የመሳሰሉ፣ ስንት ቦ ታ ሊደርሱ የሚችሉ፣ የሚያንገበግቡ ብርቅ ወጣት ልጆቿን በከንቱ ለአረመኔዎች መስዋዕት ማድረግ ነው፣ ነበር።  ከየትም ወገኑ አልወገኑ፣ እነዚህ ሰነዶች ውስጥ የሚታወሱት ሁሉ!! ከከንቱም በከንቱ የሚያደርገው ደግሞ፣ የዛሬውና የነገው ትውልድ ያለፈውን ከልቡ አጥንቶ፣ አጽንቶ ና አገናዝቦ ተገቢውን ተመክሮ ሳይወስድ፣ ዛሬም አእምሮ ቢስ ሆ ኖ የቀረ እንደሆን ነው!!!

እዚህ ሰነድ ውስጥ ያለው የመጀመሪያው ሁለት ገጽ የዚህ አእምሮ ቢስነት እንደ አይነተኛ ምሳሌ ሊወሰድ ይችላል!

በቀላል አቀራረብ ግን፣ ዓለም ከማያወቀው የማይድኑ የደዌ ዝርዝር ውስጥ  አከርካሪው “ኢ – ሕ – አ –  ፓ ”  የሚባል መጨመር አለበት፣ ያሰኛል! እውነትም ግን ዛሬ የአእምሮ  ሳይንስ የደረሰበት ለንደዚህ ዓይነት ተፈጥሮዎች የሰጠው ስምና ኪዳንም አለ! የም ሆ ነ ይህ ….እያዩ  ማለፍ …..እንደሚባለው፣  አይቶ ማለፍና   ምንም ጥርጥር የለውም፣ በየመስመሮቹ መሃል ያሉትን ሰቆቃና ስቃይ እያሰታወሱ (2*፣ የብርሃነ መስቀልንና  የኅይሌን ሰነዶች ዝርዝር ግን፣ ከገጽ 3 በኋላ ያለውን፣ የጊዜውን ሁኔት ባይነ ሕሊና እያሰቡ፣  ፖለቲካ ያገባኝ ነበር… አሁንም ያገባኛል የሚል ሁሉ አንድ ባንድ ማንበብ ያለበት ይመስለኛል።

ባለበት መሄድ ልማድ ሆኖ  እንዳይቀርብንና ሀገራችን ኢትዮጵያም እንዲሁ እንደዋዛ ከነመስዋዕት ልጆቿ  ….ዋ…. ብላ  ቀርታ እንዳትቀር!!!!

ባለበት መሄድ ልማዳችን ሆነ የሚያሰኘው፣  በተለይም የሰሞኑን የፖለቲካ ፈር / የኤርትራው ጉዞ/  ሲያስተውሉት ነው!   እሱም ሲይንስ እነዛው ጉዶች በነ ካሳ ከበደ ተመስለው  ባደባባይ በግንባርቀደምትነት  ብቅ ሲሉ ነው!

ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ ….. ተብሎ  ድሮውንም ጥንታውያን የተቀኙላት ያለምክንያት አልኖረም!

—–

*** ስዕሉ የተገኘው፣ የ ረኔ ጊራርድ / Rene Girard mimesis theory/ ማህበራዊ ጽንሰ ሃሳብ ላይ ከሚመራመር ድረገጽ ነው…..Scapegoating

*1 በተጨማሪ ስለ ሃይሌ ፊዳና ከርሱጋር መስዋዕት ሆነው ሰላለፉ ብርቅ  ኢትዮ ጵያውያን የሚከተለውን የግል ማስታወሻ ይመልከቱ (ለተጠቀሰው ጉዳይ በጊዜው የተላከ):- Project „Shading Light on Haile Fida’s Life“

*2              ……

ለነ ድንጋይ ልቡ *

ለነ ድንጋይ ልቡ (PDF)

 

ካላየህ ከልነበርክ ሕሊና ከሌለህ፣

ግድ የለም ይመችህ፤

ወሬህን አሳምር አፊዝ እሞቀህ ቤት፣

ቁስሉ የሰው ነው እንጨት ስደድበት፤

አንድ ቀንጀንበርህ የጠለቀች ዕለት

እስቲገለጽልህ ያለህበት ሌሊት

አንተም ሰው እኔም ሰው//it/… እስኪለይለት!!!

ዛሬ መጠሪያችን፣ መሃላችን ሁሉ   ይሙት  ይሙት!!!1)

አንጀትህ አንጀቴመቼስ ሊራራለት!!!

ግማሽ ጎኑ እውር ያስጫኑህ ጭንቅላት፣ የተሰጠህ መዓት!

እግዚኦ እንዳይባልልህ የለህም ሃይማኖት!

ፋላስፋ እንዳንሻ ጠላትህ ነው ትምርት!

እሪሪሪሪሪ….ለአ…...ኧረ የድንጋይ ያለህ...እንዳው. አቤት አቤት፣

ወንዝ የገጠመህለት ወዳጅህ እዚህ ነው እሱንም ጫንበት!

የማይቀረው ወንዝህ፣   እንዲያም እንዲያም ብሎ፣አዙሪቱ ታክቶት

ከለታት አንድ ቀን እሰው መንደር ደረሶ፣ሳርቀጠሉን ይዞ  እርፍ፥ እልፍ እንዲልለት!!!

*እነዚህ ከላይ ያሉት ስንኞች ብቅ ያሉት ስለነ ብርሃነ መስቀልና ሃይሌ ፊዳ

ታሪካዊ ሰነዶች / የብርሃነ መስቀል ረዳ እና የሀይሌ ፊዳ አሳዛኝ ኑዛዜዎች 

በሚል አርዕስት ሰነዶቹን  አጅቦ ስለወጣው የሚያሳፍር አስተያየት በማዘን ነው!

__________________________________________________________________________

እነ ማን ነበሩ ?

To read a few lines on torture :

http://samvak.tripod.com/torturepsychology.html

Advertisements
This entry was posted in Social & Cultural. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s