ማስተዋል ለማያቅተው

ዘረኝነት ምንድን ነው?(pdf)

racism.pdf

አንዳንዴ፣ ጊዜና ሁኔታውን ከጠበቁ አንድ ሁለት ቃላት፣  ከሺ ዓ/ ነገሮች የበለጠ በአእምሮ ውስጥ ይገቡና እውነቱን ቁጭ ያደርጉታል። 

አውሮፓውያን መቼም በዘረኝነት የተጠመቁበት ጊዜ አለፎና ተመክሮዋቸውን ሰብስበው ለራሳቸው፣ በተለይ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ፣ በሰላም ለመኖር ይሞክራሉ፤ የኋላ ኋላ ተባብረው፣ ቀደም ሲል ደግሞ  ቢያንስ በየራሳቸው መንግሥታት ሥር። በተለይም ጀርመን ስለዘረኝነት ተመክሮ ያውራ ቢባል፣ ይህ እንደማይሳነውና እንደሚችል ምንንም አያጣላም። ይህም ሆኖ  ግን አሁንም ህዝቡ ከዳር እስከዳር ከዚህ በሽታ ነጻ ነው ማለት አይደለም። ስለሆነም በስፖርት ሜዳ  ላይ ሁሉ በተለይም እግርኳስ ጨዋታ ላይ ይህ የዘረኝነት በሽታ ደጋግሞ  ይንጸባረቃል። አልፎ አልፎም ከአፍሪቃ በመጡ  ወይንም እዚህ በተወለዱ ጥቁር ተጫዋቾች ላይ የዘረኝነት ስድቡ ሲበዛ አእምሮ  ያለው ዳኛ ጨዋታውን አልመራም ብሎ እስቲያቋርጥ ድረስ ሁሉ ያጋጠማል።  በቅርቡ እንደሆነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ  አንድ የክለቡ ባልደረባ የሆነው፣ አንድ ጀርመን ሀገር የተወለደ ጥቁር ጓደኛው ላይ የሚሰነዘረውን ዘረኝነት አስመልክቶ፣ በዛሬው የጠዋት የስፖርት ሪፖርት ላይ (MOMA) ላይ እንደተዘገበው፣ አንዱ ተጫዋች በ ፌስ ቡክ (Facebook) ላይ፣ ለአስነዋሪዎቹ የዘርኝነት ስድቦቹ እንደሚከተለው ይመልሳል፣

እናንት ቅጥ ያጣችሁ ተሳዳቢዎች፣ ለመሆኑ፣ የናንት የአእምሮ ልክ (IQ)፣ እኔ ጥዋት ጠዋት ዳቦዬን ከማሞቅበት መሳሪያ (Toaster) ያነሰ እንደሆን ታውቃላችሁ! „ ፣ ሲል ሳያሽሞነሙንና ዙሪያ ገደሉን ሳይሄድ እቅጩን ነገራቸው።

በደቂቃ ውስጥ ይህን ያነበቡም የሰሙም፣

“እነዚህ ዘረኞችን እንደዚህ እቅጩን ካልንገሯቸው አደብ አይገዙም”

ሲሉ፣ በ ሺ የሚቆጠሩ ጓደኞቹና ከስፖርትም ሆነ ከሌላ ማህበራዊ ጉዳዮች ጋር የሚገናኙ ሰዎች ሁሉ፣

“እግዚአብሄር ይስጥህ! እንደዚህ እውነቱን ሳታድበሰብስ መናገርህ፣”

ብለው ደገፉት አመሰገኑት አጀቡት!

ከዚያም ውይይቱ ደርቶ፣ ይህ አስተዋይ ሰው፣ እስፖርተኛው፣ እንዲህ ሲል ደመደመና ውይይቱን ዘጋው።

ዘረኝነት፣ የአቋም፣ የሀሳብ ልዪነት አይደለም!

ዘ ረ ኝ ነ ት፣  ወ ን ጀ ለ ኝ ነ ት   ነ ው!   ብሎ  አሳረፈን!

ይህ ትልቅ ሀ ቅ ነው!  ከብዙ እንክርት፣ትንተናና ታሪክ ያላነሰ እውነቱን ፍጥጥ አድርጎ የሚያሳየን ነው!

ዛሬ በኛ የኢትዮጵያ እውነታ ውስጥ ያለውና  አቆብቁቦ መረን ሊለቅ የተሰናዳው እውነትም ይህ ነውና፣ ይህን የሚያራምዱትም ሆነ በዚህ ፈር ተጉዘው፣ ከየትም መጡ፣ ፈለቁ፣ ሄዱ፣ ቆዩ፣ ከማንም በለጡ አስናቁ፣ ሥልጣን ተከናነቡ አጡ፣ ኖሩ አሸነፉ ተሸነፉ፣ ተጎዱ ጎዱ፣ በዘረኝነት ተጠምቀው፣ ዛሬ  ሀገሪቱን  ለመዓት፣ ህዝቡን  ለመታላለቅ የሚደግሱ ሀይሎች፣ ይህን ሀቅ፣ ነገ ዛሬ ሳይሉ እንዲያውቁት ይገባል። ይህ እውነታ እሩቅ አይደለም፤ ከትላንት ወዲያ ዓለም አይቶታል፤ ትላንት አፍሪቃ ቅምሶታል! ዛሬም በመጠኑ በየአምባው የሚፈጸመው፣ የሚነገረው፣ የሚዛተው፣ ያደባባይ ምስጢር ነው፣

ዘረኝነት የአቋም ልዩነት አይደለም!

አዎ! ዘረኝነት ወንጀል ነው!

ይህ የወንጀል እሳት ከመቀጣጠሉ በፊት፣ አስተዋዩ  ኦባንግ ሜቶ  እንዳለው፣

ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!

እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!”

ስለሆነም፣ በዚህ አኳያ፣ ከሁሉም ወገን ያገባኛል፣ ይገባኛል የሚለው ያስተውል፣ ሁሉም አደብ ይገዛ።

ሃገር ሰው፣
መድሃነ፥ኢትዮጵያደወል፣/1 ይስተጋባ፣
እውነቱም ይሰማ!
(ለማንበብይጫኑ)፣

እንተባበር ፣ ሁላችንም ከዳር እስከዳር አብረን እናስብ።  ሀና አሬንድት / Hanna Arendt/ [1]የፖለቲካ ፈላስፋዋ፣ ሰለዘረኝነት ታመራምራ ጨምቃ ስታስተምርም፣ ዘረኝነት ማለት፣ ማሰብ ማቆም ነው! ነበር ያለችው!  ትክክል ናት!

ስለዚህ ባጭሩ፣ ሌባ ጣትን ወዲያና ወዲህ ከመቀሰር ይልቅ፣ ጣቶቻችንን ሰብሰብ አርገን  በአንድነት ለደግ ጊዜ እናስብ፣ እንታገል!

Harmon-palm-box


[1]The origins of totalitarianism (1958)

http://archive.org/details/originsoftotalit00aren

****

ከፍ ያለው ጽሁፍ፣ የሰሞኑ የኦሮሞና የአንድነት እንኪያ ሰላንቲያ ከመነሳቱ በፊት የተሰነዘረ ማስጠንቀቂያና የንቃትጥሪ ነበር! አሁንም ንክሻው ከመክረሩና ሁሉንም ከማጥለቅለቁ በፊትማስተዋል ለማያቅተው ሰው እውነቱን ለማወቅ ይረዳል

እስከመቼ አሻንጉሊት!nsa-rope2

ደግሞም፣ የሚከተሉት ድረ፥ገጾች ውስጥ የቀረቡት ቀላል ማብራሪያዎች ይጠቅሙ እንደሆን እንመልከታቸው! ወይስ በተንኮለኞች ቀለብ ጠግቦ አድሮ ተኝቶ፣አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም ነው !

—-
http://www.cooperationcommons.com/taxonomy/term/50
________________

ሰው ሁሉ ያም ይህን ማንበብ ስለሰለቸው፣ የዚህን ንጠረ፥ነገር፣ በአንድ ሁለት ቃላት እኔ ደግሞ ባጠቃልለውስ፥

ከበደ፣ ገመቹና  ሃጎስ እያንዳንዳቸው ለየብቻቸው ቢሠሩ ውጤታቸው፣
ከበደ – 2 ዳቦ
ገመቹ – 3 ዳቦ
 ሃጎስ – 4 ዳቦ

ሁሉም እንደችሎታው ቢሆንና ለየብቻቸው የሰሩት ቢደመር 9 ዳቦ ሆነ ማለት ነው!

በአንድነት ተባብረው ሥራቸውን አቀናጅተው ቢሠሩ ግን፣ ለምሳሌ ያህል 12 ዳቦ ሊወጣው እንደሚችል ሳይንስ የመሰከረለት ጉዳይነው።

ሁሉም እንደችሎታቸው ያገኙትን ቢከፋፈሉ 3 ዳቦ ይተረፋቸዋል ማለት ነው! እንግዲህ አምባ ጓሮው ሁሉ (አምባጓሮእንዴት ዓይነት ጥሩ ቃል ነው! አምባጉዋሮው!) እቺን 3 ዳቦ መካፈል አለመቻል ነው!

1 ዳቦ ላስተዳደር፣ ለትምህርት፣ለቸገረው ወዘተ፣ቢሰጥ፣
1
ዳቦ ለሚቀጥለው ምርት ቢከማች፣
የቀረውን 1 ዳቦ፣አሁኑኑ ካልበላሁ ከተባለ ደግሞ አስተዳደሩ ለከበደ፣ ለገመቹና ለሃጎስ ሊያከፋፍላቸው ይችላል።

ይህን ማድረግ ተስኖን፣ የሚያስማማ አስተዳደርም መመሥረት አቅቶን፥ እየተተራመስን የእሳት እራትና የባዕድ አሻንጉሊት መሆናችን፣ ያሳፍራል፣ ያስፈራል፣ አዎ በዚህ የተነሳ፣ የሚያስፈራ ጣጣ ውስጥ በዚህ በሰለጠነ ዘመን መግባታችን!

ለምንድን ነው፣ በዛሬው ዘመን ታድያ እንደዚህ ቀላል የሆነ ጉዳይ፣ለኛ ኢትዮጵያን ለመረዳትና ለመቀበል የሚያዳግተን!

ረቀቅ ማለት ካስፈለገ ደግሞ፣

ወገናዊነት ለምንጩ
 ማገላበጥ ይቻላል!

ከዚያ ያለፈው ደግሞ የትምህርት፣ቤት ተቋሞች (academic) ጉዳይ ነው!

This entry was posted in Social & Cultural. Bookmark the permalink.

Leave a comment