ሕብረ፥ቅላጼ ሲነገር …

Hibre-kilatsie-sineger-title-web

ለአንዱ ምንጭtitel

„ወገናዊነት ለምንጩ“

ለኢትዮጵያ ሀገራችን ደህንነት

*

ከየት ?

_

ህዝብ፣ ዓለም፣ ሰው ለዘመናት የተራኮተው፣ የተተራመሰው፣ አሁንም በከፊል የሚራኮተውና የሚተራመሰው አራት ትላልቅ ቁምነገሮች ላይ የሚያደርሰው ብቃት ለማግኘት ነው።

የሰው ልጅ ሰላም ይፈልጋል፣ ለብልጽግና ይደክማል፣ ለሰብዓዊ የባህል ዕድገት ይታገላል፣ መንፈሱን የሚያረጋጋበት ዕምነት ይሻል። ሰላም፣ ብልጽግና፣ ባህልና ዕምነት ናቸው፣ የሰውን ልጅ በዓለም፣ በየሀገሩና፣ በየጎራው እያሰለፉ የየራሱን ራዕይ የሚያስፈጥሩት።

ትልቁና መሰረታዊው ቁም፥ነገር፥ ማለትም፣ አቢይ ፍሬ፥ነገሩ ደግሞ፣ እነዚህ አራቱ ትላልቅ ግቦች፣ እየተደጋገፉ እንዲስተጋበሩና አንድ የጋራ ህብረ፥ፍሬ  የሚሰጡበትን እውቀትና፣ ጥበብ፤  ሰብዓዊ ባህልንና ሰላማዊ መንፈስን መካን ነው።

titelrainbow

ሕብረ፥ቅላጼ ሲነገር

*

ይሰምርለት ይሆን ሳይንስ ፍጹምነት

በአዲሱ አድማስ፣ ባየር፥ቦታ ሰዓት

ባህል እየሆነ ንፁህ ሰብዓዊነት፤

ታሪክ ሲገሰግስ፣ ላንድ አፍታ ቆም ሲል?

ለሰላም ነፃነት፣ ለአዲሱ ባህል!

ሕይወት እኮ ዕምነት ነው፣ ዕምነትም በሕይወት

ዝንተ፥ዘላለሙን፣ ከሰማይ፥ሰማያት፥

በሕብረ፥ቅላጼ ወደ ድለ፥ፋንታ፣ ዕፁብን ለማግኘት።

 

ዕ ል ል! ዕልልታ ነው የእርሱ ማሳረጊያው

በታላቁ ተስፋ፣ ምሕረቱ ነው ሕያው፤

ዕውነት ዕውነት በሉ፣ ምንጭ ይሰማዋል ሰው።

መልክተ፥ቅላጼ

HARMONY

 

ስነ፥ፍጥረት ሆነ ሰማየ፥ሰማያት

ሰው፥ልጅ ሲጥለቀለቅ በጥበቡ ሙላት

መንግሥት ታሪክ ሆኖ፣ ህጎቹ ነፃነት፣

ከዕምነት ከሃይማኖት

ንፁህ የሆነ ዕውቀት ለሚከሰትበት፣

ለመንግሥተ፥ሰማይ፣ ፍልሚያ እኮ ነው ሕይወት።

 

ለሰላም ለባሕል፣ ለፍጹማዊነት

ዕልል ዕልል እንበል፥ ለታላቁ ድርጊት!

በሕብረ፥ቅላጼ ለቅዱሱ ግብዓት

ምንጩን ይዳብሳል፣ ሰብዕ በመለኮት!

*

melikte-poem

ሁሉንም  ለማንበብና ለማገናዘብ እዚህ ይጫኑ …

*

Side

ስለ ~ሕብረ፥ቅላጼ ሲመረመር~ ተጨማሪ ሰናዶች ይቀጥላሉ …

PART I

 HIBREKILATSE-LEAIMERO-HARMONY-2012-2015-

(ሕብረ፥ቅላጼ ሲመረመር በአማርኛ)

PART II

HIBREKILATSE-LEAIMERO-HARMONY-2012-2015-

(Interpreting-the-Harmony-Model /English/

PART III

HIBREKILATSE-LEAIMERO-HARMONY-2012-2015-

(The Wheel-of-Knowledg/The Syntheses/ English)

This entry was posted in Social & Cultural. Bookmark the permalink.

1 Response to ሕብረ፥ቅላጼ ሲነገር …

  1. Pingback: ማስተዋል ለማያቅተው | ልዩ ጉዞ … liyu-guzo > the Journey > le Voyage …

Leave a comment